ካፊን በመጠኑ ያነቃቃል እና በተከታታይ ወስደዉት በድንገት ቢያቆሙ አነስተኛ የሆነ እራስምታት እና ሌሎችም አነስተኛ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊያስተናግዱ ይችላሉ። ግን አብዛኛዎቻችን ያለምንም ከባድ ችግር ካፊንን መቀነስ ወይም ማስወገድ እንችላለን።
በዓለም ላይ ብዙ ሰዎች በየቀኑ ካፊን ያለበትን መጠጥ እንደ ቡና፣ ሻይ እና ለስላሳ መጠጦች ባሉት ዉስጥ ይጠቀማሉ። ሰዎች በኮካ ኮላ ውስጥ ያለው የካፊን መጠን በተመሳሳይ የቡና መጠን ውስጥ ካለው እጅግ እንደሚያንስ ሲረዱ ብዙ ጊዜ ይደነቃሉ።
ሁሉም ሰው ካፊን ላይወስድ እንደሚችል እናውቃለን። ሁሉም ሰው በየጊዜው መወሰድ እንደማይፈልግም እናውቃለን። ሰዎች ለራሳቸው እና ለቤተሰቦቻቸው ምርጫ እንዲኖራቸው የተለያዩ ከካፊን ነጻ መጠጦችም እናቀርባለን።
ይህን ያውቁ ኖረዋል? ከካፊን ነጻ ዳይት ኮክ፣ ስፕራይት፣ ሊልት እና ፋንታን የመሳሰሉ ከካፊን ነጻ የሆኑ ለስላሳ መጠጦችን እናቀርባለን።